ሩሲያ ዩክሬንን በድሮን እና ሚሳኤል ደበደበች

Date:

ሩሲያ የአየር ላይ ጥቃት እንደፈጸመችባት ዩክሬን አስታወቀች::

ሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ነው የተባለለትን የእስረኛ ልውውጥ ማድረጋቸው ከተሰማ በኋላ የሩስያ ጦር በ 298 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 69 ሚሳኤሎች በመጠቀም ጥቃት መፈፀሙን የዩክሬን አየር ኃይል አስታውቋል።

በጥቃቱ 12 ዩክሬናውያን ሕይወታቸውን እንዳጡም ተገልጿል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ “ሩሲያ ላይ ጠንካራ ጫና ካልተደረገ ይህ ጭካኔ ሊቆም አይችልም ፤ አሜሪካም ዝምታዋን መስበር አለባት” ሲሉ ተናግረዋል።

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ለውትድርና አገልግሎት ይውላሉ የተባሉ 142 ቦታዎች ላይ ጥቃቱ ማነጣጠሩን እንደገለጸ ቢቢሲ ዘግቧል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ እለት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልፀው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እያደረጉ በሚገኙት ተግባር “ደስተኛ አይደለሁም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...