በአውሮፓ ግዙፍ የሆነውን የሊቲየም ክምችት የሚገኝበትን ስፍራ በዶንባስክ ግዛት የሩሲያ ጦር ተቆጣጥሯል ።
ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኘው ጦሩ 74 ከመቶ የዶምባስክን ግዛት መቆጣጠር ችሏል ።
ሼቭሼንኮ የተባለው ስራ በራሽያ ቁጥጥር ስር መዋሉ አሜሪካ ከኪዬቭ ጋር የገባችው የማዕድን ማውጣት ውል ‘ውሃ በላው’ ሊባል የተቃረበ ይመስላል ።
ትራምፕ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባይደን በሞኝነት ለለገሱት በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በካሳ መልክ ማዕድን አውጥተው እንዲጠቀሙ ከዩክሬን ጋር መስማማታቸው ይታወሳል ።
የኬዬቭ ሹማምንት አሜሪካ ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንድትሰጣቸው ቢማፀኑም ዋሺንግተን እንቢ ብላለች ።
ይባስ ብሎ ለአሜሪካ ሊሰጥ የነበረውን የማዕድን ማውጫ ስፍራ አሁን የሩሲያ ጦር ተቆጣጥሮታል ።
ሊቲየም ለኤሌትሪክ መኪና ባትሪ ማምረቻ ዋነኛ ግብዐት ነው ። ቻይና ይህን ምርት እየተጠቀመች የኤሌክትሪክ መኪናን በገፍ እያመረተች ነው ።
አሜሪካ እና አውሮፓም የኬዬቭን ሊቲየም ማዕድን በገፍ ቋምጠውበታል ።
ይሁን እና ዋነኛውን ስፍራ ራሽያ ይዛዋለች ። ሌላኛው የማዕድን ማውጫ ለማዕከላዊ ዩክሬይን የቀረበ መሆኑ እፍይታ ነው ። ግን እንደ ሼቭሼንኮ አይሆንም ።
