የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ አቬሮ እውቅና ለመስጠት በስታዲየሙ የሚገኘውን ዴይ ሴንተር በስማቸው ለመሰየም መወሰኑ ተዘገበ።
ከዚህ በኋላ ማዕከሉ “ዶሎሬስ አቬሮ ዴይ ሴንተር” በሚል ስያሜ እንደሚጠራ ተገልጿል።
በክለቡ የተወሰነውን ውሳኔ ይፋ የሚያደርገው ሥነ ሥርዓት ከሳምንት በኋላ በጆዜ አልቫላዴ ስታዲየም እንደሚካሄድ የፖርቹጋሉ ጋዜጣ ኤ ቦላ ዘግቧል።
የስፖርቲንግ ሊዝበን ደጋፊ የሆኑት ማሪያ ዶሎሬስ ከክለቡ ጋር ያላቸውን ትስስር በማክበር ይህ እውቅና መሰጠቱ ተገልጿል።
