ቀርጫንሼ ግሩፕና ጂሊ ሁለት ኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለገበያ አቀረቡ

Date:

ቀርጫንሼ ግሩፕ ከቻይናው የመኪና አምራች ጂሊ ጋር በመተባበር ሁለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሞዴሎችን ለኢትዮጵያ ገበያ በይፋ አስተዋውቀዋል።

ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ናፍሌት ሆቴል በተካሄደው የምርት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር፣ “ጂሊ ኢኤክስ 2” እና “ጂሊ ኢኤክስ 5” የተሰኙ ሁለት ሞዴሎች ለገበያ ቀርበዋል።

የቀርጫንሼ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እስራኤል ደገፋ ኩባንያው ላለፉት 10 ዓመታት በቡና፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግና በዓለም አቀፍ ንግድ ዘርፎች ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው፣ አሁን ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ዘርፍ መግባቱን ገልጸዋል።

ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማትና የኢነርጂ ሽግግር ስትራቴጂ ለመደገፍ፣ በውጭ ነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ፣ የትራንስፖርት ወጪን ለማቃለልና የከተሞችን አየር ብክለት ለመቀነስ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

“ጂሊ ኢኤክስ 2” ለከተማ ውስጥ ጉዞ ተስማሚና በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ ሞዴል ሲሆን፣ “ጂሊ ኢኤክስ 5” ደግሞ በቴክኖሎጂና በምቾት ደረጃ ከፍ ያለ አማራጭ መሆኑ ተገልጿል።

ቀርጫንሼ ግሩፕ ከሽያጭ በተጨማሪ የጥገና አገልግሎት፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች ስልጠናና ከኃይል አቅርቦት መሰረተ ልማት አጋሮች ጋር በቅንጅት ለመስራት እቅድ መያዙን አስታውቋል። በሸገር ከተማ በሚያካሂደው ኢንቨስትመንት ተሽከርካሪዎቹን በሀገር ውስጥ የማምረት ሂደቱን አጠናቅቆ ወደ ሥራ መግባቱንም ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቢሾፍቱ የአየር ኃይል 10 ኪ.ሜ ሩጫ ተካሄደ

2ኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ...

በአዲስ አበባ ዲፕሎማቶችና ነዋሪዎች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ተካሄደ

በአዲስ አበባ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት፣ ዲፕሎማቶች፣ የአፍሪካ...

ከንቲባ አዳነች ለትዕግሥት አሰፋ የክብር አቀባበል አደረጉ

የ52ኛው የበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድር አሸናፊ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ማንችስተር ዩናይትድ 4-0 ተሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብሬንትፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን 4-0 በማሸነፍ ድል...