በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

Date:

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል 5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...