በኢቲቪ መዝናኛ ዲፓርትመንት በከፍተኛ አርታኢ መደብ ሲሰራ የነበረው ጋዜጠኛ የኑስ መሀመድ ባላሰበው መንገድ ከስራ በመሰናበቱ በእጅጉ ማዘኑን የገለፁበት መረጃ አጋርቷል ። እነሆ ያጋራው ሙሉ መረጃ
በአማራ ክልል ለመስክ ሥራ በወጣሁበት ወቅት በታጠቁ ኃይሎች ከደረሰብኝ እገታ በኋላ ያለሁበትን ሁኔታ እና ከቴሌቭዥን መስኮት ለረዥም ጊዜ የጠፋሁበትን ምክኒያት ለማወቅ ተደጋጋሚና ተከታታይ ጥያቄዎች ደርሰውኛል።
በቅድሚያ አስባችሁ ስለጠየቃችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ። ስላለሁበት ሁኔታ መረጃው ለሌላችሁ ውድ ኢትዮጵያውያንና የፕሮግራሞቼ ተከታታዮች ሁሉ፤
ከባልደረቦቼ ጋር በሥራ ላይ ሳለን ከደረሰብን የ13 ቀናት እገታ መልስ፣ ከዚያው መከራ ጋር ተያይዞ በኢቢሲ ተቋም በኩል ማናችንም ባልጠበቅነው መልኩ ከሥራ የመሰናበቴ ደብዳቤ ደርሶኛል፡፡ እዚህም እዚያም የገጠመኝ ሁኔታ ልባዊ ሐዘን ይፈጥራል። አልሐምዱሊላህ መጽናናትን አላጣሁም።
በአሁኑ ሰዓት ምንም እንኳን ሙሉ አቅምና ጉልበት ባይኖረኝም ጉዳዩ በፍ/ቤት እንዲታይልኝ አንቅስቃሴ ጀምሬአለሁ። የሁሉም ልባዊ ወዳጆቼ ጥየቃና ድጋፍ አይለየኝ እላለሁ፡፡ ወደፊት የደረስኩበትን ሁኔታ በዝርዝር የማሳወቃችሁ ይሆናል፡፡
ጋዜጠኛ የኑስ ሙሐመድ
(ከፍተኛ አርታኢ-Senior Editor)
