በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፉ ስድስቱ ቡድኖች ታወቁ

Date:

ሊቨርፑል ፣ አርሰናል፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ኒውካስል እና ቶተንሃም በቀጣይ ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ፤ አርሰናል ሳውዝሃምተንን 2 ለ 1 አሸንፏል። ለአርሰናል የማሸነፊያ ግቦቹን ኦዴጋርድ እና ቴርኒ አስቆጥረዋል።

በኦልድትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ አስቶንቪላን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ አማድ ዲያሎ እና ክርስቲያን ኤሪክሰን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ 1 ለ 1 ሲለያዩ  ለሊቨርፑል መሀመድ ሳላህ፤ ለክሪስታል ፓላስ ደግሞ እስማኤል አሳር ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 ሲያሸነፍ ኒውካስትል በኤቨርተን1 ለ 0 ተሸንፏል።

በሌሎች ጨዋታዎች በርንማውዝ ሌስተር ሲቲን 2 ለ 0፤ ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 2 ለ ዐ፤ ቶተንሃም በብራይተን 4 ለ 1 ሲያሸነፉ  ብሬንትፎርድ ከ ወልቭስ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...