በጥቅምት ወር የምርቶች ዋጋ ከ20 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳየ

Date:

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት እየተጠናቀቀ ባለው የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዚህ ወር የዋጋ ግሽበት ካሳለፍነው መስከረም ወር ከተመዘገበው ጋር ሲነጻጸር  የ11 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በወሩ ውስጥ የሥጋ ዋጋ በ23 ነጥብ 8 በመቶ፣ የዘይትና ቅቤ በ20 ነጥብ 6 በመቶ፣ የወተት ተዋጽኦዎችና እንቁላል በ20 ነጥብ 1 በመቶ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ በ11 ነጥብ 1 በመቶ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል።

የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች የዋጋ ግሽበት 14 ነጥብ 1 በመቶ ሲደርስ ለዚህ ጭማሪ በዋናነት አስተዋጽኦ ያደረጉት ከስጋ፣ ወተት እና ዘይት በተጨማሪም የስኳር፣ ማር እና ቸኮሌት በ36 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸው ነው፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆነው የዋጋ ግሽበት 15 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ሲገለጽ የአልኮል መጠጥና ትምባሆ በ18 ነጥብ 92 በመቶ፣ ትራንስፖርት በ17 ነጥብ 1 በመቶ እና ትምህርት በ15 ነትብ 5 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸውን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ በያዝነው ሳምንት ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ሀገራዊ የዋጋ ግሽበት መጠኑ ባለበት ባለ ሁለት ድጅት ሊቀጥል እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...