አሜሪካ ስለፈፀመችው ጥቃት እስካሁን ድረስ ምን እናውቃለን

Date:

በእስራኤል እና ኢራን ግጭት ዛሬ ማለዳ ላይ ያሉ አንኳት መረጃዎችን እንዲህ ጠቅለል አድርገን አቅርበንላችኋል።

አሜሪካ ኢራን ውስጥ በሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ተቋማት፤ ናታንዝ፣ ኢስፋሃን እና ፎርዶ ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብላለች። ፎርዶ በተራራዎች ውስጥ የሚገኝ እጅግ በጣም ለመድረስ አስቸጋሪ የሆነ ተቋም እንደሆነ ይታመናል።

ትራምፕ በቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር ዘመቻውን “አስደናቂ ወታደራዊ ስኬት” ሲሉ አሞካሽተው፣ ቴህራን በፍጥነት ሰላም እንድትፈጥር ወይም “ከዚህ የባሰ” ጥቃት እንደሚደርስባት አስጠንቅቀዋል።

አሜሪካ ቢ-2 አውሮፕላኖቿን በመጠቀም ወደ መሬት ሰርስረው የሚገቡ ቦምቦችን በመጠቀም ድብደባ መፈፀሟ የተገለፀ ሲሆን የአገሪቱ መከላከያ በጉዳዩ ላይ ዛሬ መግለጫ ሊሰጥ ይችላል።

የኢራን የመንግሥትመገናኛ ብዙኃን ፎርዶ በከፊል “በጠላት ጥቃት ተፈጽሞበታል” ያለ ሲሆን፣የጉዳቱን መጠን ግን አሳንሶ አቅርቧል።
ቴህራን ቀደም ሲል አሜሪካ በሁለቱ አገራት ግጭት ውስጥ ጣልቃ የምትገባ ከሆነ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙየአሜሪካን ጦር ሠፈሮች ላይ ጥቃት እንደምታደርስ አስጠንቅቃለች።

እስራኤልየአሜሪካን ጥቃት መደሰቷን የገለፀች ሲሆን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ” እና “የታሪክንሂደት የሚለውጥ” ሲሉ አንቆለጳጵሰውታል።

በአሜሪካ ሪፐብሊካኖች የትራምፕን እርምጃ ሲያወድሱ ዲሞክራቶች ደግሞ አሜሪካ ወደ ሌላ “ማብቅያ ወደሌለው” ጦርነት እየገባች ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ኢራን አሜሪካ ለፈፀመችው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ሚሳዔሎችን መተኮሷ ተሰምቷል።
በእስራኤል እና ኢራን ግጭት አዳዲስ መረጃዎችን እና ትንታኔዎችን እንዲሁም ፎቶዎችን እናቀርብላችኋለን አብራችሁ ቆዩ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...