የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራንፕ በካናዳ የብረትና አልሙኒየም የማዕድን ዘርፍ ላይ ጥለውት የነበረውን የ25 በመቶ ግብር ወደ 50 በመቶ አሳድገውታል።
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስር አሜሪካ በካናዳ የብረት ዘርፍ ላይ የጣለችውን ታሪፍ “ህገወጥና ተገቢ ያልሆ” ነው ሲሉ ተችተዋል።
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስር ማርክ ካርኒ በዛሬው እለት የአሜሪካን ሁለተኛ ዙር የታሪፍ ጭማሬን ተያይዞ መግለጫ ሰጥተዋል።
ማርክ ካርኒ በመግለጫቸውም ፕሬዚዳንት ትራንፕ በካናዳ የአልሙኒየም እና ብረት ዘርፍ ላይ የ50 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ አድርገዋል ብለዋል ።
ይህም “ህገወጥ፣ተገቢ ያልሆ ነው ያሉ ሲሆን ለአሜሪካ ኢንዱስትሪዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ለካናዳ አጠቃላይ በጣም መጥፎ ውሳኔ ነው “ሲሉ ተናግረዋል።
ማርክ ካርኔ ካናዳ ለአሜሪካ ገበያ የአልሙኒየም እና የብረት መዓድን በማቅረብ በኩል ቁጥር አንድ መሆኗንም ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ኤፍፒ ነው።
ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
