አዋሽ ካፒታል አ.ማ. በአዲሱ የአገሪቱ የካፒታል ገበያ ማዕቀፍ በይፋ ሥራ ጀመረ

Date:

የአዋሽ ካፒታል አ.ማ.በአዲሱ የአገሪቱ የካፒታል ገበያ ማዕቀፍ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርኃ ግብር ታህሳስ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል ተከናዉኗል፡፡

የማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በተናገሩት መሰረት ሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመግባት ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋሙ ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ (subsidiary) የሆነው አዋሽ ካፒታል አ.ማ ህጉ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችና መመዘኛዎች በተገቢው ሁኔታ በሟሟላት ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክአገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቀበሉን አሳውቀዋል፡፡

በማከልም አዋሽ ካፒታል አ.ማ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በተገቢው ሁኔታ ራሱን በማደራጀት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የዝግጅት ምዕራፉን በማጠናቀቅ በሁለት መቶ ሚሊዮን ካፒታል ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

አዋሽ ካፒታል አ.ማ. የተለያዩ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎቶችን ማለትም በድርጅት ፋይናንስ እና የማማከር አገልግሎት፤ በዋስትና ንግድ እና የማገናኘት ስራ፤ በምርምር እና የገበያ ኢንተሊጀንስ ፤ በአረንጓዴ ፋይናንስ እና የESG (ከባባዊ፣ ማህበራዊና አስተዳዳራዊ) የማማከርአገልግሎት እንደሚሰጥ የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አንዱአለም ኃይሉ በማስጀመሪያ ሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡

አዋሽ ካፒታል አ.ማ ለማቋቋምና ወደ ስራ ለማስገባት ሰፊ ጥናትና ዝግጅት ሲደርግ መቆየቱ ለዚህም በታቀደው መሠረት ስራው እንዲሰራ የማቋቋሚያና የአሰራር ፖሊሲ ሠነድ ሲሰራ የቆየው ፋይዳ ኢንቨስትመንት ባንክ ተብሎ የሚጠራው የኬንያው አማካሪ ድርጅት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን እንዲሁም አዋሽ ካፒታል አ.ማ በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ከተፈቀደላቸው የኢንቨስትመንት ባንኮች ውስጥ አራተኛው ሆኖ ስራ መጀመሩን በማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል።

ድሬቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...