ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የነበራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተቀዛቀዘ ከአስር ወራት በኋላ አዲስ አምባሳደር ሾመች።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት አብዲሰላም አብዲ አሊ በ #ሞቃዲሾ በሚገኘው የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ትናንት ሰኞ እለት በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን የሱሌይማን ደደፎ የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
ሚኒስትሩ አዲስ የተሾሙትን አምባሳደር በመቀበል በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እና ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሶማሊያ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር የተሾሙት፤ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ሶማሊያ አንድ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማትን “ከዲፕሎማሲያዊ ሚናቸው ጋር በማይጣጣም መልኩ” ተሰማርተዋል ስትል ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሻከረ በኋላ ነው።
