የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እስራኤል በኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ማውገዙን አስታወቀ፡፡
ሞስኮ ጥቃቱን አስመለክቶ በሰጠችው መግለጫ በኢራን ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ድርጊት ነው ስትልም ኮንነዋለች፡፡
ጥቃቱ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ተቋም ጉዳዩን እየመረመረ ባለበት ሰዓት የእስራኤል ጥቃት ያልተገባ ነው ብላለች ሞስኮ፡፡
በቀጠናው ላይ ሰላም እንዲመጣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥረት እያደረገ ባለበት ሰአት የኔታንያሁ መንግስት የፈጸመው ደርጊት ተቀባይነት የለውም ስትል ሩስያ አጋርነቷን ለኢራን አሳይታለች ተብሏል፡፡
ዘገባው የአር ቲ ኒውስ ነው
