በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና የሠራተኛ ቅነሳ ዕቅድ እንደሌለ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ኮሚሽነሩ እንዳብራሩት፣ የመንግሥት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ዋና ዓላማ ሠራተኞችን መቀነስ ሳይሆን ብቃታቸውን፣ ክህሎታቸውንና የሥራ አፈጻጸማቸውን ማሳደግ መሆኑን ጋዜጣ ፕላስ ዘግቧል።
በፌዴራልና በክልል ደረጃ ከ6.5 ሚሊዮን በላይ የመንግሥት የሥራ መደቦች መለየታቸውን፣ ከእነዚህም 2.3 ሚሊዮን ያህሉ በሠራተኞች የተያዙ ሲሆን፣ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ የሥራ መደቦች ግን ክፍት እንደሆኑ ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም፣ የሪፎርሙ ትኩረት የሠራተኛ ቅነሳ ሳይሆን የሠራተኞችን ብቃት ማጎልበትና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ማረጋገጥ መሆኑን አረጋግጠዋል።
