ከሞት በኋላ የአካል ክፍል ንቅለ ተከላን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው

Date:

ከሞት በኋላ ኩላሊትና ጉበትን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ልገሳና ንቅለ ተከላ ህክምናን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጤናዬ ደምሴ፣ በኢትዮጵያ ከሞት በኋላ የአካል ክፍል ልገሳና ንቅለ ተከላ በህግ የተፈቀደ ቢሆንም በተደራጀ መልኩ ወደ ስራ አለመግባቱን ገልጸዋል፡፡

ህክምናውን ለማስጀመር የሚያገለግሉ መሳሪያዎችና ማሽኖች እየተደራጁ እንዲሁም በቂ የሰለጠነ የሰው ሀይል እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ንቅለ ተከላው በሆስፒታሎች የሚከናወን በመሆኑ ሆስፒታሎችን ዝግጁ ለማድረግ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን መመሪያም መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

በመመሪያው መሠረት የአካል ክፍል ለጋሽ ፈቃደኝነቱን በጽሁፍ ማረጋገጥ ወይም በኑዛዜ ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን፣ ፈቃዱን በማንኛውም ጊዜ የማንሳት መብትም አለው፡፡ ለጋሹ ግን አካል ክፍሉን የሚቀበለውን ሰው የመምረጥ መብት እንደሌለው ተመላክቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቡሌ ሆራ መሶብ አንድ ማዕከል 54 የመንግሥት አገልግሎቶችን ለመስጠት ዝግጁ ሆነ

በደቡብ ኦሮሚያ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ የተገነባው መሶብ አንድ...

13ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ኅዳር 12 ይካሄዳል

13ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ኅዳር 12 ይካሄዳል 13ኛው...

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ክስ ዳግም እንዲታይ ተወሰነ

ከሦስት ዓመት በላይ በፍርድ ቤቶች ሲከራከር የቆየው የተንዳሆ ስኳር...

በአራት ወራት ከ2,472 ኪ.ሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታና ማሻሻያ ተከናወነ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት...