ኬንያ እና ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማገናኘት ሁለት ድልድዮችን ሊገነቡ እንደሆነ ነው የተነገረው ፡፡
ሁለቱ ሀገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ በዳዋ ወንዝ (ራሃሙ እና ሱፍቱ) በኩል ለአካባቢው ማህበረሰቦች የጤና ፣ የትምህርት እና የገበያ መዳረሻን ለማሳለጥ የሚያግዙ ድልድዮች እንደሚገነቡ አስታውቀዋል።
ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይሰጣሉ የተባሉትን ድልድዮች ሁለቱ ሀገራት በጋራ እንደሚገነቡት ፒዩፕል ዴይሊ ዘግቧል ፡፡
