ወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኬሞ ቴራፒ ህክምና ጀመረ

Date:


   

ወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ከጀመረ ሁለት ሳምንት የሆነው ሲሆን በተወሰኑ ታካሚዎች የካንሰር ህክምና መስጠቱን ገልጿል:: ህክምናው ከመጀመሩ በፊት ወረፋ የያዙ ስለነበሩ ከተጀመረ ጀምሮ ለስምንት ሰዎች ህክምና መሰጠቱን ገልፀዋል::

የኬሞ አገልግሎት ለሁለት ሰው የተሰጠ ሲሆን ሁለት ዓይነት የኬሞ ቴራፒ ሂደት ሲኖር የአንዱ እጥረት እንዳለ በወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ሀምዛ እህመድ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል::

አሁን ላይ ለሳምባ እና ለጡት ካንሰር ታካሚዎች ህክምና የሰጠው ሆስፒታሉ የቀረውን መድኃኒት ካገኘ 80 በመቶ በሚባል ደረጃ ለሁሉም ካንሰሮች ህክምና እንደሚሰጥ ዶክተር ሀምዛ ገልጸው ይሁን እንጂ የጎደለው መድሀኒት እያለም አሁን ላይ ለጡት ካንሰር ህክምና ሙሉ በሙሉ እየሰጠ እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡

የካንሰር ህክምና ሶስት ዓይነት እንደሆነ የገለፁት ዶክተር ሀምዛ የቀዶ ፣ የኬሞ ቴራፒ ህክምና እና የጨረር ህክምና ሲሆኑ ሆስፒታሉ አሁን ላይ የጨረር ህክምና እንደማይሰጥ እና ከዛ  ወጪ ያሉትን ህክምናዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል ::

የካንሰር ህክምና የረዥም ጊዜ ክትትል የሚወስድ ሲሆን እንደየደረጃው ከአምስት እስከ አስር ዓመት እንደሚወስድ ተናግረዋል:: በተለይ በአዳጊ ሀገራት የማህበረሰብ የካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ የሚሰሩ ስራዎች መጓደል እና እሱን ተከትሎ የሚኖር ደረጃው የገፋ የካንሰር ህመም ከፍ ያለ ነው ሲሉ በወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ሀምዛ እህመድ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል::

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...