47 ታሪኮችን የያዘውና “ዥዋዥዌ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የደራሲ ሕይወት እምሻው ስድስተኛ መጽሐፍ ሕዳር 6 2018 ዓ.ም ተመርቆ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።
ደራሲዋ ስለ አዲሱ መጽሐፏ<< ዥዋዥዌ አርባ ሰባት የዘመን ማስታወሻ ታሪኮችን የያዘ ሲሆን የተስተካከለና የተመሰቃቀለው፤ የተሳካና የተሰናከለው፤ የሚያምርና የሚያስቀይመው፤ የሚያስደስትና የሚያማርረው፤ የሚያኮራና የሚያሳፍረው ዘመነኛ ኢትዮጵያዊ ሕይወታችንን እንደ ወረደ የሰነድኩበት ነው›› ስትል ተናግራለች።
የ “ዥዋዥዌ” መጽሐፍ ምርቃት ቅዳሜ ህዳር 6 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው አዲሱ የጃፋር መጽሐፍት መደብር ውስጥ ይከናወናል።
ሕይወት እምሻው ከዚህ በፊት አምስት መፅሐፍትን ማለትም ባርቾ፣ ፍቅፋቂ፣ ማታ ማታ፣ ለእርቃን ሩብ ጉዳይ እና የቡና ቁርስ ለአንባቢያን ያደረሰች ደራሲ ነች።
