የቱሪዝም ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እየቀነሱ ነው

Date:

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮችን ተከትሎ በቱሪዝም ዘርፍ የመማር ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ይህንን የገለጹት የፌደራል ሆቴል እና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም መምህራን እና አመራሮች ናቸው፡፡

ጣቢያችን ያነጋገራቸው የተቋሙ መምህራን እና አመራሮች ለሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ፍላጎቱ ያላቸው በርካታ ወጣቶች ቢኖሩም ባለው የፀጥታ ስጋት ለቱሪዝም ቅርበት ያላቸው ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ላይ እየገቡ ነው ብለዋል።

ይህ የፀጥታ ችግር በጎብኚዎች ላይ ከሚፈጥረው ተፅእኖ በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ሰልጥነው ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋቱ ተፈጥሯዊ ነው ብለው የሚያምኑ ቢሆንም ነገር ግን ይህ የፀጥታ ችግር ዘላቂ ስለማይሆን ወደ ቱሪዝም ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባም ጭምር አሁን ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ በመግለፅ ሌሎች የቱሪዝም ዘርፍ የስራ አማራጮችን ማየት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...