የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ 81.8 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አስመዘገበ

Date:

​የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ በ2017 በጀት ዓመት የ81.8 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ማስመዝገቡን በዓመታዊ ሪፖርቱ ይፋ አደረገ። ይህ ኪሳራ ያጋጠመው ለቴክኖሎጂ፣ ለባለሙያዎች ቅጥር እና ለገበያ መሠረተ ልማት የተደረገው ከፍተኛ መነሻ ኢንቨስትመንት ገና በጅምር ላይ ካለው የሥራ ገቢ በመብለጡ መሆኑ ተገልጿል።

​እንደ ሪፖርቱ መረጃ፣ ኩባንያው በዓመቱ 126 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 119.8 ሚሊዮን ብሩ (ከ95% በላይ) የተገኘው ከተከፈለ ካፒታል ወለድና ከሌሎች ገቢዎች ነው።

ከዋናው የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አገልግሎት ማለትም ከኩባንያዎች ምዝገባ እና ከአባልነት ክፍያ የተገኘው ገቢ 6.1 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑ የገበያው እንቅስቃሴ ገና በጅምር ላይ መሆኑን ያሳያል።


​የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር)፣ ያለፈው ዓመት ኢትዮጵያ የተደራጀ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ለመመሥረት የመጀመሪያውን ተጨባጭ እርምጃ የወሰደችበት ታሪካዊ ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓመቱ ውስጥ 174.4 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በዋናነት ለዘመናዊ የንግድ ሥርዓቶች እና ለባለሙያዎች ልማት የዋለ መሆኑ ተጠቁሟል።

​የሥራ አፈፃፀሙን በተመለከተ፣ ከብሔራዊ ባንክ ጋር በመተባበር የተጀመረው የባንኮች የእርስ በእርስ የገንዘብ ገበያ ከ820 ቢሊዮን ብር በላይ የግብይት መጠን አስመዝግቧል። በተጨማሪም ወጋገን ባንክ እና ገዳ ባንክ የመጀመሪያዎቹ ተመዝጋቢ ኩባንያዎች ሆነዋል፤ የኢትዮ ቴሌኮም ምዝገባም ተቀባይነት አግኝቷል።

​በቀጣይ አምስት ዓመታት (እስከ 2029) ESX ቢያንስ 50 ኩባንያዎችን ለመመዝገብ፣ 3 ሚሊዮን ግለሰብ ባለሀብቶችን ለማሳተፍ እና የገበያ ካፒታሉን 1 ትሪሊዮን ብር ለማድረስ ትልቅ ግብ አስቀምጧል።

በተጨማሪም በ2029 ኩባንያው ራሱ በገበያ ላይ አክሲዮኑን ለሕዝብ በማቅረብ (Self-listing) በባለሀብቶች የሚመራ ተቋም ለመሆን አቅዷል።@SECO

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...