የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአውሮፕላን እጥረት የተነሳ ዕድገቱ 15 በመቶ መብለጥ እንዳልቻለ ተነገረ

Date:

የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በአሁን ወቅት ባጋጠመው የአዉፕላን እጥረት ምክንያት የዓመታዊ የተሳፋሪዎች ቁጥር ዕድገቱ ከታቀደው በታች መሆኑን አስታወቀ።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በቅርቡ ከብሎምበርግ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ላይ እንዳስረዱት፣ አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከ12 እስከ 15 በመቶ የሚደርስ የሁለት አሃዝ ዕድገት እያስመዘገበ ነው።

​አቶ መስፍን ይህንን አስመልክቶ ሲናገሩ፦ “አሁን ባለው ሁኔታ በአውሮፕላን እጥረት ምክንያት ዕድገታችን ከ15 በመቶ በላይ መሆን አልቻለም። ይህ እጥረት ባይኖር ኖሮ ከ15 በመቶ በበለጠ ፍጥነት እናድግ ነበር” ብለዋል።
​
የአቅርቦት መስተጓጎሉ በዋነኝነት የሚታየው ሰፊ አካል ያላቸዉ አውሮፕላኖች ላይ ሲሆን፣ ይህ ሁኔታ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሊቀጥል እንደሚችል አመላክተዋል።

​ይሁን እንጂ፣ አየር መንገዱ ከሁለት ዓመታት በኋላ ከዋና ዋና አምራቾች የሆኑትን ቦይንግ እና ኤርባስ ጨምሮ በርካታ ሰፊ አካል አውሮፕላኖችን በብዛት ለመቀበል መታቀዱን ገልጸዋል።

ይህ አዲስ ግዥም የአጭር ጊዜ ዕድገት መገደብን በመቀልበስ የረጅም ጊዜ ዕድገት ዕቅዱን ለማሳካት ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...