የፈረንሳይ ከተሞች ሌሊቱን በሰዓት እላፊ ገደቦች

Date:

ቅዳሜ እና እሑድ በመላ አገሪቱ የተከሰተውን ሁከትና ዘረፋ ተከትሎ በበርካታ የፈረንሳይ ከተሞች ውስጥ የተጣሉ የሰዓት እላፊ ገደቦች፣ ሌሊቱ በአንጻራዊ ሰላም እንዲያልፍ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲያን ለኮርኑ ተናገሩ።

ተቃዋሚዎች ቅዳሜ እና እሁድ ተሰባስበውበት የነበረውን ፕላስ ደ ላ ሬፑብሊክ እና የሌይ አል የገበያ አካባቢን ጨምሮ፣ በማዕከላዊ ፓሪስ በሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ገደቦች ተጥለዋል።

በደቡባዊ ፈረንሳይ በሚገኙት ማርሴይ፣ ቦርዶ፣ ኒስ እና ሊዮንን ጨምሮ በሰሜኖቹ ሊልና ሌሎች ከተሞች፣ የወጣቶችን እንቅስቃሴና መሰባሰብ የሚገድቡ ሌሎች እርምጃዎችም ተግባራዊ ሆነዋል።

የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኮርኑ እርምጃዎቹን ላስፈፀሙ የፖሊስ አባላት ምስጋና አቅርበው፣ ማክሰኞ ምሽት ተጨማሪ የሰዓት እላፊ ገደብ የሚጣሉባቸው ቦታዎች ጉዳይ እንደ አስፈላጊነቱ እንደሚወሰን ገልፀዋል።

ለኮርኑ በኤክስ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ውሳኔዎቹ በየአካባቢው ባለው ሁኔታ መሠረት በፈረንሳይ የክልል ባለሥልጣናትና በአካባቢ ከንቲባዎች እንደሚወሰኑ አስገንዝበዋል።

ቅዳሜ እና እሁድ በነበረው ሁከት በርካታ ንብረት የተዘረፈ እና የወደመ ሲሆን ከ2,500 በላይ ሰዎች ታስረዋል። ወደ 1,000 የሚጠጉ የፖሊስ አባላትም ቆስለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ...

የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

  የሥርዓተ ቀብር መረጃ:- የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት...

የዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት...

በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ነበረበት

በግዢ ሂደት ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የላቦራቶሪ ማረጋገጫዎች የከፋ የጥራት...