የፑቲን አስፈሪ መግለጫ

Date:

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የመጀመሪያው  መጠነ ሰፊ ዖሪሺኒክ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል  ስርዓት ምርት መጠናቀቁን አሳወቁ ።

የመጀመሪያው መጠነ ሰፊ ምርት ሂደትን ያለፈው እና የተመረተው ዖሪሺኒክ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ስርዓት በሩሲያ ጦር ወደ ስራ መግባቱን ፑቲን   ይፋ አድርገዋል።

ለምዕራቡ ዓለም አስደንጋጩ  መረጃም መሆኑም አይቀሬ ነው።

በዩክሬን ምድር ስላለው ወታደራዊ ዘመቻ አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ  ማብራሪያ ሲሰጡ ነው ይህን ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን።

ሩሲያ ህዳር ላይ ዖሪሺኒክን በመሞከር ዓለምን ጭንቀት ውስጥ እንድትገባ ማድርውጓም አይዘነጋም።

የሚሳዔል ስርዓቱ ኑክሌር አረር ጫፍ መሽከም የሚችል እንደሆነም ይታመናል።

ቀደም ሲል ፑቲን ሚሳዔሉ በመደበኛ የጦር መሳሪያነት አቅሙ ከዝቅተኛ የኑክሌር ፍንዳታ ጋር የሚስተካከል ውድመት ያስከትላል በሚልም አረጋግጠው ነበር።

ሩሲያ ህዳር ላይ በዩክሬንዋ ከተማ ኒፕሮ ላይ ዖሪሺኒክን ሞክራ ለሶስት ሰዓታት ያህል የፍንዳታው ቃጠሎ መቆየቱ ይታወሳል።

ዘገባው የአር ቲ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...