ተበዳይ እህታችን ፍትህ አገኘች

Date:

እህታችን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ፣ በ3 ግለሰቦች በመንገድ ላይ እየተጎተተች ስታለቅስ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት ሲዘዋወር ነበር

ወ/ሮ መካ መሃመድ አራጋው ትባላለች። ሪያድ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከታዩን መረጃ አድርጓል:-

“መካ መሃመድ አራጋው፣ ከ4 ወር በፊት በስራ ኮንትራት ወደ ሳዑዲ የመጣች ዜጋችን ነች። 
በሪያድ የ ኤምባሲ ቪዲዮው እንደተሰራጨ በዕለቱ (July 17,2025 በቪዲዮው ማስረጃነት ለሳዑዲ መንግስት የፀጥታ አካላት ባቀረበው አቤቱታ መሠረት፣ ድርጊቱን የፈፀሙት በቁጥጥር ስር ማዋልና ተበዳይ ከለላ እንድታገኝ፣ ጉዳዩም በህግ እንዲያዝ በማድረግ እና ዜጋችን ለደረሰባት ጉዳት ተገቢውን ካሳ ተቀብላ መብቷ ተከብሮ ወደ ሀገሯ እንድትመለስ ከመግባባት በተደረሰው መሠረት፣ በኤምባሲያችን በአካል ተገኝታ የተወሰነላትን የ 20,000 የሳዑዲ ሪያል የገንዘብ ካሳ ተረክባለች።

ሚሲዮናችን፣ ዜጋችን ፍትህ እንዲታገኝ መረጃውን በማጋራት ለተባበሩ ዜጎች እንዲሁም ለሳዑዲ መንግስት የፍትህ አካላት ምስጋና እያቀረብን፣ የዜጎቻችን መብት ለማስከበር በሚደረገው ጥረት የማህበረሰቡ ትብብር እና ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን።

  #የዓባይልጅ #EslemanAaby

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...