ዩቲዩብ ለይዘት ፈጣሪዎች ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ከፍሏል

Date:

የቪዲዮ ማሰራጫው ዩቲዩብ ከ2021 ወዲህ ለይዘት ፈጣሪዎቹ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ክፍያ መፈፀሙን አስታውቆ ከ100 ሺህ ዶላር በላይ የሚሰሩ የዪቲዩብ ቻናሎች ቁጥር በአመት በ45 በመቶ እየጨመረ ነው ብሏል።

የዩቲዩብ የፕሮዳክት ኦፊሰር የሆኑት ጆሃና ቮሊች የይዘት ፈጣሪዎች “ባህልና መዝናኛን አስበን በማናውቀው መንገድ ቅርፅ እያስያዙ ነው” ብለዋል።

ዩቲዩብ ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ አገልግልቶችን ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።

ዩቲዩብ ከአጫጭር ቪዲዮዎቹ ጋር በተያያዘ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያም ሲያመጣ ሰዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት እገዛ የተቀረፀ ቪዲዮን ወደ ተቀነባበረ ቪዲዮ መቀየር ፣ ሙዚቃ መጨመርና ድምፅ መጨመር ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪ ከተፈቀዱ ቪዲዮዎች የተወሰዱ ንግግሮችን ወደ ሙዚቃ ቀይረው መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ዩቲዩብ አክሎም የጎግል VEO 3 ከዩቲዩብ የአጫጭር ቪዲዮዎቾ(Shorts) ጋር እንዲቀናጅ እንደሚደረግ ለተጠቃሚዎቹ አብስሯል።

በተጨማሪ ዩቲዩብ በአንድ ቪዲዮ በርካታ ሰዎች አንድ ላይ ሰርተው ቪዲዮ ለሁሉም ሰዎች ተመልካቾች የሚደርስበትን የ’YouTube collab’ እንደሚጀምር ገልጿል።

የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ተመልካቻቸው እንዲረዱ የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ቻትቦትም እንደሚጀምር ተገልጿል።

በመጪው ሚያዝያ ወር 20 ዓመት የሚሞላው ዩቲዩብ በመተግበሪያው ከ20 ቢሊየን በላይ ቪዲዮዎች ሲኖሩት ለበርካቶችም የገቢ ምንጭ ሆኗል።

በተለያየ መንገድ ራሱን እና ተጠቃሚዎችን ለመጥቀም እየሰራ ያለው ዩቲዩብም በ2026 ከሰፊ ማስፋፊያ ጋር እንደሚመጣ ተዘግቧል።

የመረጃው ምንጮች CNBC እና The Wrap ናቸው።

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...