በሀገር አቀፍ ደረጃ የጤና መድህን አገልግሎትን በፍትሃዊነት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና ከአምርፍ ጤና አፍሪካ ጋር በመተባበር በ2018 የእቅድ አተገባበር ላይ ያተኮረ መድረክ በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ላምሮት አንዱአለም በመድረኩ ላይ እንዳሉት፥ በሀገር ደረጃ 63 ሚሊየን ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ በቀጣይ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ ክልሎች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ባለፈው ዓመት አገልግሎቱን ለማቅረብ ከተገልጋዮች ከተሰበሰበው 19 ቢሊየን ብር በተጨማሪ 7 ቢሊዮን ብር በመንግስት መሸፈን ተችሏል።
