አንዳንድ ዲሞክራት ሕግ አውጭዎች አሜሪካ የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ የፈፀመችውን ድብደባ ያለ ኮንግረስ ይሁንታ የተፈፀሙ ናቸው ሲሉ አወገዙ።
የኮንግረስ አባሏ አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ ኮርትዝ ይህ ሕገ መንግሥቱን እና የኮንግረሱን ሥልጣን “በከባድ ሁኔታ መጣስ” እና “ፍፁም እናግ ልጽ በሆነ መልኩ ክስ ለመመስረት የሚያስችል ነው” ብለዋል።
በኤክስ ገጻቸው ላይ “ለትውልድ ሊከተለን የሚችል ጦርነት ለመክፈት በግዴለሽነት አደጋ ላይ ጥለውናል” ብለዋል።
የአሜሪካ የኮንግረስ አባሏ ራሺዳ ተላይብም የአሜሪካን ሕገ መንግሥትን “በግልፅ መጣስ” ያሉትን ድርጊት አውግዘው ኮንግረስ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።
“በመካከለኛው ምሥራቅ ለአስርት ዓመታት የተካሄደው ማለቂያ የሌለው ጦርነት የት እንዳደረሰን አይተናል፤ሁሉም በ”ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ” ውሸት ላይ የተመሰረተ ነበር። ዳግም በዚያ መንገድ አንታለልም” ብለዋል።
ሌላኛው የኮንግረስ አባል ጂም ማክጎቨርን በበኩሉ ሁኔታውን “እብደት” ብለውታል።
“ትራምፕ ኢራንን ያለ ኮንግረስ ይኹንታ ደብድበዋል፣ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ጎትቶናል። አሁንም መማር ያለብንን አልተማርንም?”
