“ ጠዋት ከ80 በላይ፤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት አርብ ድረስ ከ500 በላይ ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ” – የወላጆች ኮሚቴ

Date:




በማይናማር በእገታ ከነበሩ በርካታ ዜጎች መካከል፣ “ ጠዋት (ማለትም አርብ) ከ80 በላይ ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ” ሲል የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ ትኬታቸው ጊዜው ስላለፈ 15ዐ ዶላር ሊቀጡ ነበር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጣቱን አንስቶላቸው ነው የመጡት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለአየር መንገዱ በቀረበው የትብብር ጥያቄ ” ብሏል።

“ ከማይናማር ወደ ባንኮክ የባስ መምጫ ወጫቸውንም የኢትዮጵያ መንግስት ነው የሸፈነላቸው ” ሲል ገልጿል።

ኮሚቴው ምን አለ ?

“ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ 80 ልጆችን ለማመላለስ ፕሮግራም ተቀምጧል። ፕሮግራሙ የተቀመጠው ኒውዴይሊ ባለመው ኤምባሲ፣ ኢትዮጵያን ወክለው ታይላንድ ያሉ ሰዎች ከአርሚዎች ጋር በመነጋገር ውጪ ጉዳይ ባደረገው ጥረት ነው።

እስከ ቀጣዩ ሳምንት አርብ ከ500 በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚገቡ፣ ትኬታቸው አክቲቭ የሆነ፣ ፓስፖርት ያላቸው፣ ፓስፓርት ያላቸው ሆኖም አመት ያለፈውን ጭምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊያመጣቸው በተጠየቀው መሠረት እየተሰራ ነው።

የሚቀሩት ትኬት የሌላቸው/አጋቾቹ ፓስፓርታቸውን የቀሟቸው ወደ 78፤ ትኬት የሌላቸው በአጠቃላይ ከ200 በላይ ልጆች ከሳምንት በኋላ ፕሮሰስ እንደሚጀመር ኒውዴይሊ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይና ባንኮክ ያለው ቅርንጫፍ አረጋግጦልናል።

ማይናማር ያሉት ዜጎች መንግስት ወጪ ያወጣባቸው ከዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው በተለያየ ሥራ የነበሩ ናቸው አእምሯቸውም ጉልበታቸውም እየተበዘበዘ ያሉትና መንግስት ማስመለሱ ትክክለኛ እርምጃ ነው።

ወጣቶቹ በአገራቸው ተመራምረው የፈጠራ ባለቤቶች እንዲሆኑ፣ ሰርተው ተለውጠው ሀገርና ቤተሰብ እንዲለውጡ ምክርና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ነው ለመንግስት የምናሳስበው።
በአሁኑ ወቅት ታግተው ከአሰሪዎች ካሞፓኒ ያልወጡ ልጆች አሉ፤ አንድ ካምፕ ውስጥ 26 አሉ። አንዱን እየደበደቡት አይኑ ጠፍቷል።

ሦስት ልጆች ደግሞ/ሁለት ሴቶችና አንድ ወንድ አንድ ካምፓኔ ውስጥ አሉ። 14 ልጆች ደግሞ ቢጂኤፍ የሚባል ካምፕ ውስጥ እየተገረፉ፣ እየተቀጠቀጡ አሉ።

ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያውያኑን ባዶ እግራቸውን በጀሪካ ውሃ አሸክመው ኮረት ላይ እያስኬዷቸው እግራቸው ተላልጦ መራመድ አቅቷቸውም፤ እየተሸከሙ ወስደው ኮሚፒዩተር ላይ ሥራ እንዳሰሯቸው ሰምተናል።

ሙሉ መረጃ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰጥተናል። አሁንሞ የኢትዮጵያ መንግስት ቶኪዮ ካለው ኤምባሲ ጋር በመነጋገር  ይድረስላቸው፤ ወላጆች ሰቆቃቸውን እየሰማን ተጨንቀናል። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...