ሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 120 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ሥር ዋለ

Date:

ሚያዝያ 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተደረገ ክትትል እና ፍተሻ መነሻውን መቀሌ ባደረገ በፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ታንከር ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 120 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ሕገ-ወጥ ዶላሩ በቁጥጥር ሥር የዋለው ምንም ፈሳሽ ጭነት ሳይጭን ወደ አዲስ አበባ መስመር እየተጓዘ በነበረ የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ታንከር ውስጥ በፕላስቲክ እና በፕላስተር ተጠቅልሎ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በዚህ ድርጊት የተሳተፉ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ሕገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ፤ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ሕብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...