ፊፋ ክለቦቹ ክሳቸዉን እንዲያቆሙ ወሰነ

Date:

መቻል፣ ሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለቦች ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት የወሰዱትን የክስ ጉዳይ በተመለከተ ከFIFA የተሰጠ ውሳኔ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ጥሰት የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን ተከትሎ ክለቦቹ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ውሳኔው ታግዶ እንዲቆይ በፍርድ ቤት መደረጉ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ጉዳዩ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ማምራቱ የፌዴሬሽኑን የመተዳደርያ ደንብ እና በአባልነት የታቀፈበት የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር (FIFA) መተዳደርያ ደንብ የሚጥስ በመሆኑ ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም እና ግንቦት 7/2017ዓ.ም ለዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር (FIFA) በተፃፈ ደብዳቤ ስለጉዳዩ አሳውቀናል።

በመሆኑም የፌዴሬሽናችንን ደብዳቤ ተከትሎ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር (FIFA) ግንቦት 29/2017ዓ.ም በላከው ደብዳቤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ FIFA መተዳደርያ ደንብ አንቀፅ 14-1 እና አንቀፅ 19 መሠረት የሚከሰቱ ጉዳዮችን ያለ ሦስተኛ አካል ጣልቃ ገብነት እና በነፃነት የመመልከት ግዴታ እንዳለበት ገልፆ ያለ ፌዴሬሽኑ እውቅና (ፌዴሬሽኑ በድርጊቱ ተሳታፊ ባይሆን እንኳን) የሚከናወኑ ድርጊቶችን ጨምሮ በእግር ኳሳዊ ውዝግቦች ላይ የሚኖሩ ማናቸውም የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት በአንቀፅ 14 ላይ የተጠቀሱ ህግጋትን የሚጥስ በመሆኑ ለቅጣት እና እገዳ እንደሚዳርግ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደርያ ደንብ አንቀፅ 65 ላይ እንደተጠቀሰው በፌዴሬሽኑም ሆነ አባላቱን፣ ክለቦቹን፣ ተጫዋቾቹን፣ ባለሙያዎቹን እና ሊጎቹን የሚመለከቱ ውዝግቦች መደበኛ ፍርድ ቤቶች ሳይካተቱበት በብቸኝነት ወደሚፈታው ሎዛን የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ሊመራ እንደሚገባ ይገልፃል።

በመሆኑም የፌዴሬሽኑን እና የፊፋን መተዳደርያ ደንብ በጣሰ መልኩ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት የወሰዳችሁትን ጉዳይ በአስቸኳይ በማቆም፤ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔን ተግባራዊ እንድታደረጉ በጥብቅ እያሳሰብን፤ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ የጀመራችሁትን ክስ ስለማቆማችሁ የሚገልጽ ማስረጃ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት እንድታቅረቡ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

@EthiopiaFF

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...