የጂቡቲው ፕረዚዳንት እስማኢል ኦማር ጊሌህ በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕረዚዳንቱ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከዛሬ ጳጉሜ 2 እስከ ጳጉሜ 5 መሆኑን ተገልጿል።
በዚህ ቆይታቸውም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ላለው የካሪቢያን – አፍሪካ እና የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የሚታደሙ ይሆናል።
በተጨማሪም ከፕረዚዳንቱ ገጽ በተገኘ መረጃ መሰረት “ከእነዚህ ሁለት ጉባዔዎች በተጨማሪ፣ ማክሰኞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ይፋዊ ምረቃ ላይ ይሳተፋሉ” ሲል አስታውቋል።
