ሱስ ማለት አንድን ነገር፣ ተግባር፣ እጽን፣ በተደጋጋሚ ተጠቅሞ ነገር ግን ማቆም አለመቻል ባለመቻላችን አካላዊ ፣ ስነ ልቦናዊ ፣ እንዲሁም ኢኮኖምያዊ ጉዳት እና ተጽእኖ ሲያሳድር ነው። ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች መተው አለበት የተባለውን ነገር አብዝቶ ለማድረግ መፈለግ፣ ከሱስ ውጪ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ማጣት፣ ተደጋጋሚ ቃላትን መናገር፣ አለባበስ መዛባት ( በተገቢው ንጽህናን አለመጠበቅ)፣ የምግብ ፍልጎት መዘጋት፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው ተግባቦት መቀነስ፣ የድብርት ስሜት ስሜት ይሰማል፡፡ በሚያቆሙ ጊዜ ወዲያው የሚታዩ ሁኔታዎችም የስጋት ስሜት ፣ እንደገና ወደ ሱሱ የመመለስ ጉጉት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ መነጫነጭ (የባህሪ መለዋወጥ)፣ ማጥወልወል፣ የድካም ስሜት መሰማት ወዘተ ናቸው፡፡
መፍትሔዎቹ፡- የሥነ ባሕሪ ሕክምና እና ምክር ማግኘት፤ የመድሃኒት ሕክምና ማግኘት፤ ተያይዝው የሚመጡ የስነ አእምሮ ለውጦች የስነ አእምሮ ሕክምና ማግኘት፤ ተመልሰው ወደ ሱሱ እንዳይገቡ የማገገሚያ ክትትል ማድረግ፤እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የአፍንጫ አለርጂ (Nasal Allergy)
የአፍንጫ አለርጂ እንደ አስም ሁሉ ትክክለኛ መንስሔው ባይታወቅም በሽታውን በሚቀሰቅሱት ወይም በሚያባብሱት ሁኔታዎች እንዲሁም በበሽታው አጠቃላይ ባሕሪና ዕድገት ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ በሽታው የሚገለፀው በማስነጠስ፣ውሃ የመሰለ የአፍንጫ ፈሳሽ፣አፍንጫን ማፈን ዓይንና ጉሮሮን ማሳከክ ፣ዕምባ መፍሰስ ፣ራስ ምታት በድንገት በመቀስቀሱናሲያሰኘው ደግሞ ያለምንም መድኃኒት ለጊዜው በመልቀቁ ነው፡፡ ብዙን ጊዜ በሽታው የሚቀሰቀሰው በአበባ ብናኝ፣ ፣የውሻና የድመት ዕዳሪ፣ ሽቶ፣አቧራ፣ኬሚካል፣የሰው ጠረን፣የጫማ ሽታና እንዲሁም በቅዝቃዜ በሽንት ቤትና በከብቶች በረት ነው፡፡ የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ማድረግ ከችግሩ ለመውጣት ይረዳል
1. የታዘዘን መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ
2. ውሃ አፍልቶ ባዶውን ወይም በባህር ዛፍ መታጠን
3. ውሃና ጨው አፍልቶ በአፍንጫ መሳብ
4. በሽታውን የሚቀሰቀሱ ወይም የሚያባብሱ ነገሮችን ማስወገድ
5. ከተቻለ የሥራና የመኖሪያ አካባቢን መቀየር
6. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየቀኑ መሥራት
7. በብርድ ጊዜ አፍንጫን መወተፍ ወይም መሸፈን
8. ድመት ወይም ውሻ ከነኩ በኃላ ወዲያውኑ እጆን መታጠብ፡፡
ደረቅ ሳል ዓይነተኛ ምልክታቸው
አስም፡- አስም የምንለው የመተንፈሻ ትቦ ሊያብጥና በማበጡም ሲጠብ የሚፈጠር ነው፡፡ተያይዞም እነዚህ ምልክቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ፡- ሲርታ ድምጽ መሰማት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ውጋት፣ ሳል ከእንቅልፍ የሚረብሽ፡፡
ቃር፡- ይህ ችግር የጨጓራ አሲድ ከመጠን በላይ በመመረቱ ወደላይ (ወደ ምግብ ትቦና ጉሮሮ) ሲመለስ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ ይህ አሲድ ሳል እንዲቀሰቀስ ያደርጋል ተያይዞም፡- የደረት ማቃጠል፣ የምግብ / ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስ፣ ረጅም ጊዜ የሚስተዋል ደረቅ ሳል፣ ጉሮሮ አካባቢ ያበጠ ስሜት መሰማት፣ የድምጽ መቀየር፡፡
የቫይረስ ኢንፌክሽን፡- እንደ ጉንፋን፣ ኮሮና የመሳሰሉት ቫይረሶች ደረቅ ሳልን የማስከተል አቅም አላቸው፡፡
ለኬሚካሎች እና ብናኞች መጋለጥ፡- ይህ ሁኔታ በስራችን/በአካባቢያችን ተጋላጭነት ካለ አለርጂን በመፍጠር ደረቅ ሳልን ያስከትላሉ፡፡
አንዳንድ ለሌላ ሕመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች፡- ትክትክ በተለይ በሕጻናት ላይ፣ የሳንባ ካንሰር፣ የልብ ድካም፣ የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) ተያይዞ ያሉ ምልክቶች፣ ለሶስት ወይም ከዚያ በላይ ሳምንታት ማሳል፣ የደረት ሕመም፣ በሚተነፍሱበት ወቅት ወይም በማሳል ወቅት የደረት ሕመም፣ ክብደት መቀነስ፣ ድካም፣ ትኩሳት፣ የምሽት ላብ፣ ብርድ ብርድ ማለት የመሳሰሉት በዋነት ይጠቀሳሉ፡፡
ደረቅ ሳልን ለመከላከል፡-
በጨው መጉመጥመጥ፦ በመጠኑ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ አንድ ማንኪያ ጨው በመጨመር ቀና ብለን ጉሮሯችንን እንዲያጸዳ በማድረግ መጉመጥመጥ ደረቅ ሳልን ለመከላከል ወይም በቀላሉ ለማስቆም ይችላል።
ፍራፍሬዎችን አዘውትሮ መመገብ፦ ፍራፍሬዎችን በጭማቂ መልክም ይሁን ጥሬያቸውን አዘውትሮ መጠቀም ፍራፍሬዎቹ በውስጣቸው ባለው ንጥረ ነገር አማካኝነት ለደረቅ ሳል እንዳንጋለጥም ይረዱናል።
አረንጓዴ ሻይ፦ አረንጓዴ ሻዩን በሻይ ቅጠሉ ማሸጊያ ጀርባ ላይ ባለው አጠቃቀም መሰረት ካፈላን በኋላ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጨምሮ መጠጣትም ደረቅ ሳልን ለማከም ፍቱን ነው። የአረንጓዴ ሻይ እና የማር ጥምረት ደረቅ ሳልን ከማከም ባሻገርም በደረቅ ሳል ወቅት የሚከሰቱ የጉሮሮ ሕመሞችንም ለማከም ይረዱናል።
የዝንጅብል ሻይ፦ በፈላ ሻይ /ከተገኘ አረንጓዴ ሻይ/ ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ዝንጅብል በመጨመር መጠቀምም ለደረቅ ሳል መፍትሔ ነው።
