በኢትዮጵያ 3.8 ሚልየን ዓመታት እድሜን ያስቆጠረ የራስ ቅል መገኘቱ ተገለፀ

Date:

በኢትዮጵያ 3.8 ሚልየን ዓመታት ዕድሜን ያስቆጠረ የኦስትራሎፒቴከስ አናሜንሲስ ዝርያ የኾነ የራስ ቅል መገኘቱ ተገለፀ። በአፋር ክልል ሚሌ አካባቢ መገኘቱ የተገለፀው ቅሪት አካል በዓለም አቀፍ አንትሮፖሎጂስቶች ቡድን የካቲት 2008 ዓ.ም. እንደተገኘ ማወቅ ተችሏል። የተገኘው የራስ ቅል ከዘመናዊ የሰው ልጅ ጋር ተዛማጅነት ካላቸው ቀደምት የኦስትራሎፒተከስ ዝርያዎች አንዱ የሆነው የኦስትራሎፒቲከስ አናሜንሲስ እንደኾነም ተነግሯል። ኦስትራሎፒቲከስ አናሜንሲስ ከዚህ ቀደም የሚታወቀው በመንጋጋ አጥንቶች፣ በተቆራረጡ ጥርሶች እና ጥቂት በተሰበሩ የእጅ አጥንቶች ሲኾን ይህ በተመራማሪዎቹ የተገኘው የራስ ቅል ሙሉ በመኾኑ የአውስትሮሎፒቲከስ አናሜንሲስ ዝርያ ምን እንደሚመስል ለማወቅ እንደሚረዳቸው እምነት ተጥሎበታል። የአውስትራሎፒትከስ አፋርነሲስ ዝርያ የኾነችው ሊሲ (ድንቅነሽ) በአፋር ክልል ሃዳር አካባቢ በፈረንጆች 1974 እንደተገኘች ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...