
ቋቁቻ የተለመደና በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው፡፡ የተለያዩ ምልክቶች ያሉት ሲኾን ቋቁቻ በአብዛኛው ጀርባ፣ አንገት፣ ደረትና የላይኛው የእጃችን ክፍል አካባቢ ይወጣል፡፡ ጠቆር ያሉ (hyper pigmented)፣ ነጣ ያሉ (hypo pigmented) አንዳንዴም ቀላ ያሉ ክብ ወይም እንቁላል ቅርጽ(oval) ሽፍታዎች ሲኖሩት እነዚህ ሽፍታዎች ላይም ትንንሽ ቅርፊቶች ይታያሉ፡፡ ሽፍታዎቹን በጣታችን ስንለጥጠው ወይም ፋቅ ፋቅ ስናረገው ቅርፊቶቹ በደንብ ይጎላሉ፡፡ የተለመደ ባይሆንም አንዳንዴ የማሳከክ ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡
ምን ዐይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል?፡– በአብዛኛው በወጣትነት እና በጎልማሳነት የእድሜ ክልል ውስጥ ይከሰታል፡፡ ለቋቁቻ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች አሉ፡፡ በዋናነትም በተፈጥሮ ተጋላጭነት (genetic predisposition) ይህም በቤተሰብ አባላት ውስጥ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሞቃታማ አካባቢ መኖር፣ የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም፣ እርግዝና፣ ቆዳችን ወዛም ከሆነ፣ Oily የሆኑ ቅባቶችን መጠቀም፣ ከመጠን ያለፈ ላብ ለቋቁቻ ያጋልጣል፡፡
ቋቁቻ እንዴት ይታከማል?፡–
ሽፍታው በቆዳ ሐኪም ታይቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሐኪሙ በሚያዘው መሰረት በሚቀባ፣ በሻምፖ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ህክምናው ይሰጣል፡፡ ከህክምናው በኋላ ሽፍታው ላይ የነበሩት ቅርፊቶች ይጠፋሉ፤ ይህም የህመሙን መዳን ያመለክታል፡፡ ነገር ግን ሽፍታው ወጥቶበት የነበረው ቦታ ወደ መደበኛው የቆዳችን ቀለም ለመመለስ ሳምንታትን/ወራትን ሊወስድ ይችላል፡፡
ቋቁቻ ከሰው ወደሰው ይተላለፋል?፡– ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም፡፡ ለቋቁቻ መንስኤ የሆኑት የፈንገስ አይነቶች(በጥቅሉ Malassezia ተብለው ይጠራሉ) ከቆዳችን ጋር ተስማምተው የሚኖሩ (normal flora) ሲሆኑ ለህመሙ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወደ በሽታ አምጪነት የሚቀየሩ ናቸው፤ለዚህም ነው ህመሙ ደጋግሞ የሚከሰትብን፡፡
እንዴት እንከላከለው?፡– ቋቁቻ ደጋግሞ የሚከሰትብን ከሆነ እና በተለይም በሞቃታማ አካባቢ የምንኖር ከሆነ ከቆዳ ሐኪም ጋር በመመካከር ህክምናውን በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት ወይም በወር አንድ ጊዜ ለተወሰኑ ወራቶች በመውሰድ ቋቁቻ የሚመላላስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል፡፡ በጨማሪም Oily የሆኑ ቅባቶችን አለመጠቀም፣ ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መልበስ(በተለይ ከውስጥ የምንለብሳቸው) ሰውነታችን ላይ የሚጣበቁ ልብሶችን አለማዘውተር፡፡
ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
የመካንነት ጠቋሚ ምልክቶች
የአብዛኛው ጥንዶች ጥያቄም ነው አብዛኛውን ጊዜ ሰውነታችን ለምን እንደሆነ ባልጠረጠርነው መልኩ መሃንነትን ይጠቁመናል እነዚህን ምልክቶች ልብ ይበሉዋቸው አንዳንዶቹ በምርመራ የሚታወቁ ናቸው። ከ15 – 20 % የሚሆኑ ጥንዶች ለመውለድ እየሞከሩ ሳይሳካላቸው ይቀራል። ችግሩ ከሁለት አንዳቸው በኩል አሊያም ከሁለቶም ሊሆን ይችላል። እርግዝና የማይፈጠርበት ጠቋሚ ምልክቶች ይኖራሉ፡፡ ጠቋሚ ምልክቶች በሴቶች ላይ
• የሚዛባ የወር አበባ መኖር ወይም አለመኖር
• ከፍተኛ ህመም ወይም ደም ምፍሰስ በወር አበባ ጊዜ ፦ ይህም endometriosis መኖር ምልክት ሊሆን ስለሚችል
• በሰውነት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሆርሞኖች መዛባት
• በግንኙነት ሰአት ህመም ምኖር
ጠቋሚ ምልክቶች በወንዶች ላይ
• የግንኙነት ፍላጎት ምቀነስ
• የወንድ የዘር ፍሬ ላይ ህመም ወይም እብጠት መኖር
• የብልት ያለመቆም ችግር
• የወንድ የዘር ፍሬ ያለመርጨት ችግር
• የወንድ የዘር ፍሬ ማነስ እና መጠንከር
በሁለቱም ላይ ሊታይ የሚችል
• እድሜ
• ከፍተኛ ክብደት መኖር
• ማጨስ
• አልኮል መጠጣት
• በአባላዘር በሽታ ተጠቅተው ሚያቁ ከነበር
• ጭንቀት ካለ
• የተመጣጠነ ምግብ ማይመገቡ ከሆነ
የጨጓራ ሕመም
የጨጓራ ህመም አብዛኛውን ከአመጋገባችን ጋር ተያይዞ ይመጣል ስለሆነም በቤታችን ውስጥ እንዴት ማከም እንደምንችል እነሆ መረጃ፣
1. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት
2. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ
3. ዝንጅብል -አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡
4. እርጎ -በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡
5. ድንች – ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት
6. ውሃ – በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት
7. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…
8. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን
ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ
9. ቆስጣ እና ካሮት – የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት
10. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም
11. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ
12. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
13. ስጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም
14. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም
15. ቡናና ሻይ መቀነስ
16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ
17. ቅመማ ቅመም መቀነስ
18. ከዛሬ ጀምረው ይተግብሩት፣ ለሌሎችም ያጋሩ