ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በሕይወተ ሥጋ የተለየን አንጋፋው የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፕሮዲውሰር የነበረው ያየህ ይራድ አላምረው፥ በሕይወት ዘመኑ ያሰባሰባቸውን በዓይነትም በቁጥርም በርካታ መጻሕፍት፣ የጽሑፍ እና የሙዚቃ ኅትመት ውጤቶችን፣ ቤተሰቦቹ በስሙ ለኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ያበረክታሉ።
ተቋሙም እነዚህን የአርቲስቱን ውድ ስብሰቦች በልዩ ኹኔታ ራሱን የቻለ በስሙ የተሰየመ የንባብ ክፍል በማዘጋጀት በልዩ ክብር ይረከባል።
ስለኾነም፥ እነዚህን ውድ የመጻሕፍት እና የኅትመት ውጤቶችን በይፋ ለመረከብ፥ረቡዕ ታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ፣ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ዐዲሱ ሕንጻ ላይ በተዘጋጀው ልዩ የርክክብ መርኀ ግብር እርስዎም እንዲገኙልን በአክብሮት ተጋብዘዋል።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት።
