በባህርዳር ከተማ 47 ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች እየተገነቡ እንደሚገኝና አንዳንዶቹ ተጠናቀው ወደ ሥራ መግባት መጀመራቸውን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ ባህርዳር በኮሪደርና በጣና ዳር ልማት ፕሮጀክቶች አማካኝነት አዲስ ገጽታ እየተላበሰች ሲሆን፣ ይህም ለጎብኚዎችና ለኢንቨስትመንት ይበልጥ የተመቸች እንድትሆን አድርጓታል።
ከተማዋን ጽዱ፣ ውብና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ የአገልግሎትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ከንቲባው አክለውም ከተማዋ አካባቢ ጥበቃን ዘመናዊ ያደረገች በመሆኗ ከውጭ የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ገልጸው፤ ባህርዳርን ለነዋሪዎች፣ ለጎብኚዎችና ለባለሀብቶች ምቹ የመኖሪያና የሥራ ከተማ የማድረግ ራዕይ ተሰንቆ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ሆቴሎች መጠናቀቅ የቱሪዝም መሠረተ ልማቱን በማጠናከር ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ አስገንዝበዋል።
@ጋዜጣ_ፕላስ
