በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያውኩ ተግባራት በተሰማሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ከባድ ወንጀሎች ቀንሰዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሕዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል። 

ኮማንደር ማርቆስ በኤፍኤም አዲስ 97.1 አሼ ታለንት የመዝናኛ እና የመረጃ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት፥ በሕብረተሰቡ ዘንድ በተሰራው ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በከተማዋ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በ43 በመቶ ቀንሰዋል። 

በከተማዋ በተከናወኑ የአደባባይ በዓላት እና የጎዳና ላይ ዝግጅቶች የወጣቶች ሚና የጎላ እንደነበር ኮማንደር ማርቆስ ገልጸው፤ የከተማዋ ወጣቶች ወንጀሎችን በመከላከል ከጸጥታ አካላት ጋር ለሚያደርጉት ትብብር ፖሊስ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።

ባለፉት 9 ወራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ በተሰሩ ሥራዎች፣ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የወንጀሎች መነሻ ናቸው ተብለው በተለዩ 6 ሺህ 128 የሺሻ እና የጫት ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ወንጀል እንዲቀንስ አንዱ ምክንያት መሆኑን ነው የተናገሩት።

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያውኩ ተግባራት በተሰማሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው ያሉት ኮማንደር ማርቆስ ፤ በዚህ ሕግ የማስከበር  ሥራ ሕብረተሰቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸዉን ኢቢሲ ዘግባል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...