በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጋዜቦ አካባቢ እየተገነባ በሚገኝ ህንፃ ላይ በደረሰ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታዉቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ እንደገለጹት 3ቱ ሰዎች እየተገነባ ከሚገኝ ህንጻ በመዉዳቃቸዉ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ በደረሰዉ አደጋ መንስዔና የጉዳቱ ዝርዝር ሁኔታ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኝ ተገልጿል።
