በአጠቃላይ እስካሁን ባለው 67 የሚደርሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል

Date:

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮበመዲናዋ በ19 ስጋ ቤቶችና በ6 የግንባታ እቃዎች መሸጫ ሱቆች ላይ በተካሄደ ኦፕሬሽን 32 ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል፡፡

ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈጽሙ የተገኙት ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ለአንድ ቀን በተደረገ የኦፕሬሽን ተግባር ነው።

መርካቶን ጨምሮ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ባካሄደው የተጠና የኦፕሬሽን ተግባር በ2 የንግድ ዘርፎች በድምሩ 32 የንግድ ድርጅቶች በሕግ የተጣለባቸውን የደረሰኝ አጠቃቀም ግዴታ ባለመወጣት ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ተብሏል።

በዚህም ከድርጊቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው የንግድ ስራዎቹ ባለቤቶችና ሽያጩን ያለደረሰኝ ሲያከናውኑ የነበሩ ሰራተኞች የመንግስትን ግብር ለመሰወር ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተገኝተው በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን ቢሮው አሳውቋል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት በተደረገ ኦፕሬሽን በሁለት የንግድ ዘርፎች በቁጥጥር ስር ከዋሉት 32 ሰዎች በተጨማሪ ከእዚህ ቀደም የተያዙ 35 ነጋዴዎች በድምሩ 65 ነጋዴዎች ጉዳያቸው በህግ ተይዞ ማስረጃ የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን የቢሮው የኮምዩኔክሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ አሳውቀዋል።

አቶ ሰውነት ” የኦፕሬሽን ስራዎቹ ዘርፍን መሰረት እያደረግን በሚደርስ ጥቆማ እና በጥናት ላይ በመመስረት የሚካሄዱ ናቸው ” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ በዝርዝር ምን አሉ ?

” የኦፕሬሽን ስራዎች ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ናቸው ከዚህ ቀደምም በተሽከርካሪ ጎማ ሽያጭ ላይ፣ እንደዚሁም ደግሞ በኮንስትራክሽን ግብአት ሽያጭ እና በኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሽያጭ ላይ በተከታታይ የሆኑ የኦፕሬሽን ስራዎች ሲሰሩ ነበረ።

በእነዚህም በአጠቃላይ እስካሁን ባለው 67 የሚደርሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ማስረጃዎች ተጣርተው ለአቃቤ ህግ ተልኮ ክስ የመመስረት ሂደት ነው በቀጣይ የሚኖረው።

እንደዚህ አይነት የቁጥጥር ስራዎች ቀጣይነት ይኖራቸዋል ከዚህም በኋላ ተጠናክሮ ነው የሚቀጥለው።

በተለያዩ ዘርፎች ትኩረት አድርገን ነው ስራዎችን እየሰራን ያለነው መጀመሪያ በተሽከርካሪ ጎማ ነጋዴዎች ላይ ነው ያደረግነው፣ ቀጥለን በኤሌክትሮኒክስ ምርት ላይ በተሰማሩት ላይ፣ በኮንስትራክሽን ግብአቶች ላይ አሁን ደግሞ በስጋ ቤቶች ላይ ቀጥለናል።

የኦፕሬሽን ስራዎቹ ዘርፍን መሰረት እያደረግን በሚደርስ ጥቆማ እና በጥናት ላይ በመመስረት የሚካሄዱ ናቸው ስለዚህ በቀጣይም ተመሳሳይ የሆኑ እርምጃዎች መወሰዳቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...