በዚህ እጅግ ዋልጌነት በተሞላበት ስብከት ማዘኔንም ማፈሪንም…ዮናስ ጎርፌ

Date:

ጊዜው ከሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት አራት ቀን በኃላ ነው። ግሎባል አልያንስ የሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ በቦርድ አባልነት እሳተፍ ነበርና በሻሸመኔ ከተማ ውስጥ የደረሰውን ውድመት አይቶ እርዳታ ለማድረግ ወደዛው ሄደን ነበር። ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ተወያየን፣ የነደደችውንም ከተማ ተዘዋውረን አየን።


በማግስቱ ጥዋት አንድ የተቃጠለ ግሮሰሪ ፊት ቁጭ ያለ አንድ የአራት ወይም የአምስት አመት ልጅ ጉያው ሽጉጥ ያለ ልጅ የያዘ ፍጹም ምንም አይነት ስሜት በፊቱ ላይ የማይነበበ ጉስቁልና ፊቱንም ሰውነቱንም ያደቀቀው ሰው ኩርምት ብሎ ቁጭ ብሎ የተቃጠለውን ቤት ያያል። የሆነ ነገር እንዲመጣ ወይም እንዲወጣ የሚጠብቅ ይመስላል። ጥቂት ሰወች ከበውት በታላቅ ሀዘን ያዩታል። የሚያልቅሱም ነበሩ። እኛም ጠጋ ብለን ነገሩን ለማጣራት ጠየቅን።


ሰውየው ለአካባቢው እንግዳ ነው። በዛ በተቃጠለው ቤት ውስጥ መኖር ከጀመረ ገና አራት ወይም አምስት ቀን ነው። በኃላ እንዳጣራንው። ሙሉ ስሙን እንኳን በትክክል የሚያውቅ የለም። ከደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል እንደመጣ አንዳንዶች ይናገሩ ነበር፣ ለዛም እርግጠኛ አይደሉም። ሁለት ሴት ልጆቹና ሚስቱ በዚያ ቤት ውስጥ ተቃጥለው ሞተዋል።

እንደ ሀገራችን ባህል ድንኳን ተክሎ አብሮት ሀዘን የሚቀመጥ አንድ እንኳን የሚያውቀው ሰው የለውም። ቀን ቢያልፍልኝ ብሎ የመጣ ምስኪን ደሀ ነው። ከሰውየው ፊት የሚወርድ ዘለላ እንባ የለም። አንዲት ቃል ከአፉ አይወጣም። ዝም ብሎ ልጁን ከጉያው ሸጉጦ በድን መስሎ ተቀምጧል።

እንግዲህ በጋሻው ይህንን ሰው ነው እግዜብሔር ፍርዱን አመጣብህ ያለው። ይህንን ሰው ነው ቁጣው ነደደብህ ያለው። ሆስፒታል ስንጎበኝ በደረሰባት አደጋ ምናልባት እስከ እድሜ ልክ መጨረሻዋ አይነ ስውር የምትሆንን ሕጻን ልጅ ልቅሶና የናቷን ሳጋ የሚያብስ የጠፋባት እናትን ነው የፈጣሪ ቁጣ ተንቦገቦገብሽ ያለው።


ለእኔ የገባኝ የክርስቶስ መልእክት ግን ምህረቱ ከልጅ ልጅም ልጅም ነው። እሱ እኔ ሰባ ጊዜ ሰባ በቀን ምህረት እንዳደርግ ያሰተማረኝ ጌታ እሱማ 700 ጊዜ 700 በቀን ምህረት ሊያደርግልኝ፣ በጸጋውና በጸጋው ብቻ በፈሰሰው በዚያ ደሙ እንደሚያየኝ ቃሉን በሰጠኝ በእሱ እታመናሉ።

በእኒድህ አይነት ዋልጌ ሰባክያን የኦርቶዶክስ ወደሞቼና እህቶቼ ሁላችንንም እንዳታዩን በጌታ ስም እለምናለሁ። በሰው መሞት የሚሳለቅ ወንጌልም አስተምህሮትም የለንም። በአርሲም ሆነ በሌሎቹ ቦታዎች በየጊዜ የሚገደሉ ኦርቶዶክሳውያን በክርስቶስ የእኛም ወንድሞችና እህቶች ናቸ።

ይህን ድርጊት የእኛ መሪዎች ከእናንተ መሪዎች በበለጠው ጮኸው ባወገዙ ምንኛ ደስ ባለኝ። ድሮም ህዝብ ለህዝብ ተጋግዞና ተከባብሮ ነው እንጂ የኖረው የፖለቲካውም ሆነ የሀይማኖቱ መሪዎች ብዙ ጊዜ ቀናውን ሲያደርጉ ማየት ዘበት ነው። ታሪክም ለዚህ በተደጋጋሚ ምስክር ነው።

በዚህ እጅግ ዋልጌነት በተሞላበት ስብከት ማዘኔንም ማፈሪንም ደግሞም ያለሁበት ቤተ እምነት መሪ አልባ፣ ድምጽ አልባ፣ ፍትህ አልባ በምሆኗም አዝናለሁ። ሌላው ቢቀር በግሌ ሀዘኔን፣ ቁጭቴን ሳልገልጽ ማለፍ አልፈልግም።

መንግስት ሆይ ፍትህ በደጅህ ትጮሃለች!!!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...