በፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የ60 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ተቃውሞ ገጠመው

Date:



በፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የቀረበው የ60 በመቶ የክፍያ ጭማሪ በወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ትምህርት ቤቱ የላንቻ ቅርንጫፍ እንዳይዘጋ በሚል ሰበብ ጭማሪውን በግዴታ ለመጫን ሞክሯል በማለት ለካፒታል ቅሬታ ያቀረቡት ወላጆች፣ ሂደቱ ህጋዊ አሰራርን ያልተከተለና ስነ-ልቦናዊ ጫና የበዛበት ነው ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የሰሚት እና የሌሎች ቅርንጫፎች ወላጆች እንደገለጹት፣ በትምህርት ቤቱ የቀረበው አማራጭ “ወይ ጭማሪውን ተቀበሉ አለያም የላንቻ ቅርንጫፍ ይዘጋል” የሚል አስገዳጅ ይዘት ያለው ነው። ይህም በወላጆች ላይ የስነ-ልቦና ጫና በመፍጠር እና ህጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን ጭማሪው 60 በመቶ ቢባልም፣ “የክፍያ ማመጣጠኛ” በሚል በሚደረግ ማስተካከያ አጠቃላይ ክፍያው ለአንዳንድ ወላጆች ከ120 በመቶ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል።

capital news

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...