በፓርላማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረቡ ጥያቄዎችና ሀሳቦች

Date:

በ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችና ሀሳቦች አቅርበዋል።

በጥያቄዎቹ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል የታክስ ገቢ አሰባሰብ፣ የታክስ ጫና፣ ሕገ-ወጥ የገቢ ድብቅ አሰራሮችና በገቢ አሰባሰብ ሂደት የሚታዩ ብልሹ አሠራሮች ይገኙበታል። የታክስ አሰባሰብን ፍትሐዊና ውጤታማ ለማድረግ፣ ሌብነትን ለመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎችም ተጠይቀዋል።

በተጨማሪም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በመቅረፍና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን በማረጋገጥ ያስገኘው ውጤት፣ የሀገሪቱ የውጭ ዕዳ ክፍያ አቅም እንዲሁም የምንዛሪ ተመን ለውጥን ተከትሎ የተከሰቱ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ጫናዎችን ለማቃለል የሚደረጉ ጥረቶች ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ተጠይቋል።

በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በየ10 ዓመቱ መካሄድ የሚጠበቀው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ አለመካሄዱ በበጀት ድልድል፣ በልማት ዕቅድና በምርጫ ክልሎች ክፍፍል ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ በማንሳት፣ ቆጠራው የሚካሄድበት የተወሰነ የጊዜ ገደብ እንዲቀመጥለትም ጥያቄ ቀርቧል።

በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያና በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን በአስቸኳይ ለመፍታት መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ ማብራሪያ እንዲሰጥበት የምክር ቤቱ አባላት ጠይቀዋል።

ነፃ ፕሬስና የሚዲያ ተቋማት የመንግሥትን ተጠያቂነት በማረጋገጥ፣ የሰብዓዊ መብቶችን በመጠበቅና የፖለቲካ ምኅዳሩን በማስፋት ረገድ ያላቸው ሚና እንዲጠናከር፣ መንግሥት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ጉዳዩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ውስጥ እንዲካተት ጥያቄ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዳኛው በአወዛጋቢ ውሳኔዎች ከሜዳ ተሰናበተ

በእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ 2 ውድድር ላይ የተካሄደ ጨዋታን ይመራ...

ሩሲያ ከሶቪየት ዘመን ወዲህ ከፍተኛውን የወታደራዊ በጀት አጸደቀች

ሩሲያ ከሶቪየት ህብረት ውድቀት ወዲህ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለ የወታደራዊ...

ካይሮን በጭስ የሸፈነው ከባድ የእሳት አደጋ

በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በተከሰተ ከባድ የእሳት አደጋ ቢያንስ...

በባንክ በኩል ቤት በየወሩ እየከፈሉ የሚገዙበት የሞርጌጅ ሥርዓት በቅርቡ ሊጀመር ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዜጎች በባንክ በኩል ቤት...