ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ከቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር በጋራ እንዲሰሩ በር የሚከፍት መመሪያ አወጣ

Date:

ብሔራዊ ባንክ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ባንኮች ፣ ማይክሮ ፋይናንሶች እና የክፍያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር አዳዲስ የፋይናንስ ቴክኖሎጂዎችን በሀገሪቱ ገበያ እንዲሞክሩ የሚያስችል አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።

“የቁጥጥር ማዕቀፍ መመሪያ ቁጥር FS/01/2026” የሚል ስያሜ የተሰጠውና ከህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው ይህ መመሪያ ዘመናዊ የፋይናንስ ፈጠራዎች በነባር ሕጎች ማነቆ ሳይታገዱ በብሔራዊ ባንክ ጥብቅ ክትትል ስር በተወሰነ የሙከራ ምህዳር ውስጥ እንዲፈተሹ የሚያደርግ ነው።

እስካሁን ባለው አሰራር በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሕግጋት ውስጥ በግልጽ ያልተደነገጉ አዳዲስ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን ወደ ገበያ ለማስገባት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። አዲሱ መመሪያ ግን የሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው የፋይናንስ ተቋማት ከቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር አጋርነት በመፍጠር ቴክኖሎጂዎቹን እንዲሞክሩና ዘመናዊ አሰራሮችን እንዲተገብሩ ሕጋዊ ዕድል ፈጥሯል።

በመመሪያው መሰረት ወደዚህ የሙከራ ምህዳር ለመግባት የሚያመለክቱ ተቋማት እና የቴክኖሎጂ አጋሮቻቸው የሚያቀርቡት ፈጠራ የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያሰፋ ፣ የአገልግሎት ወጪን የሚቀንስ እና በነባር ሕጎች ምክንያት በቀጥታ ስራ ላይ መዋል ያልቻለ መሆኑን ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል።

በተጨማሪም ተቋማቱ በቂ የፋይናንስ አቅም ፣ የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም የሳይበር ደህንነትንና የደንበኞችን የግል መረጃ የሚጠብቅ አስተማማኝ ስርዓት መዘርጋታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።

ብሔራዊ ባንክ በሙከራው ሂደት የደንበኞች መብትና ገንዘብ እንዳይጎዳ ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል። በዚህም መሰረት በሙከራ ደረጃ ላይ ባሉ አገልግሎቶች የሚሳተፉ ደንበኞች ስለ አገልግሎቱ ምንነት እና ሊኖሩ ስለሚችሉ ስጋቶች ቀድመው በግልጽ መረጃ እንዲያገኙና ፈቃደኝነታቸውን እንዲሰጡ መመሪያው ያስገድዳል።

የሙከራ ጊዜው ሲጠናቀቅ ብሔራዊ ባንክ የቴክኖሎጂውን ውጤታማነት እና ደህንነት ገምግሞ ፈጠራው ሙሉ የስራ ፈቃድ እንዲያገኝ ወይም ነባር የፋይናንስ ሕጎች እንዲሻሻሉ የሚያደርግ ሲሆን ውጤታማ ሆኖ ካልተገኘ ደግሞ  እንዲቋረጥ ያደርጋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...

የኦዲት ጉድለት በታየባቸው ተቋማት ላይ ተጠያቂነት ለማስፈን እንደሚሠራ ተገለጸ

በኦዲት ግኝቶች የሚታዩባቸው ተቋማት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት እንደሚሠራ...