ኢሎን መስክ ለኢራናውያን ኢንተርኔት በነጻ አቀረበ

Date:

የአሜሪካው ቢሊየነር ኢሎን መስክ ንብረት የሆነው የሳተላይት ኢንተርኔት አቅራቢ ስታርሊንክ፤ ለኢራናውያን ከክፍያ ነጻ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት አቀረበ።

የኢራን መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የኢንተርኔት አቅርቦት በማቋረጡ ምክንያት በሳተላይት ለሚሠራው ለስታርሊንክ ወርሃዊ ክፍያ እየፈጸሙ ይጠቀሙ የነበሩ ኢራናውያን አገልግሎቱን በነጻ እንዲያገኙ መፍቀዱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን ስታርሊንክ በኢራን ውስጥ ሕገወጥ ቢሆንም፣ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በድብቅ አገልግሎቱን እንደሚጠቀሙ ዘገበው ጠቁሟል፡፡

የኢራን መንግሥት ከሚሰጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ቁጥጥር የሚያደርግበትን ስታርሊንክን ሲጠቀሙ የሚገኙ ሰዎች እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ሦስት ሳምንት የሞላውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በመላው ኢራን ኢንተርኔት የተዘጋ ሲሆን፣ ባለሥልጣናትም ዜጎች ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ ለማገድ የስታርሊንክ ማገናኛ የሳተላይት ሳህኖችን እያሰሱ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...