የቀድሞው ታዋቂ ተጫዋች አስቻለው ደሴ ህልፈተ ህይወት ተሰምቷል።
አስቻለው ደሴ በ1960ዎቹ ለኢትዮጵያ ወጣት፣ ተስፋ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድን፣ ለሸዋ ምርጥ እንዲሁም ለአንድነት (አዋሽ ምንጭ) እና ጳውሎስ ቡድኖች ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በ1961 ከኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ጋር የምስራቅ አፍሪካ ውድድርን ማሸነፍም ችሏል።
ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ባለ ድንቅ ክህሎት ተጫዋቾች አንዱ የነበረና በዘመኑ በአብዶ ችሎታው በእግር ኳስ አፍቃሪያን ልብ ውስጥ መቀመጥ የቻለ ተጫዋች ነበር።
ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናት ይሁን!!
ምስጋናው ታደሰ
ዝነኛው ተጨዋች አረፈ
Date:
