በትግራይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥልጣን መራዘም በክልሉ ያሉ ችግሮችን እንደማይፈታ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ

Date:

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ የሥልጣን ዘመን ለአንድ ዓመት መራዘሙ በክልሉ የተከሰቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን ከመሠረቱ አይፈታም ሲሉ አስታወቁ።

ፓርቲዎቹ  አስተዳደሩ ባለፈው አንድ ዓመት ያሳየው አፈጻጸም ደካማ በመሆኑ የሥልጣን ዘመኑ እንዲራዘም የተደረገበት መንገድ አከራካሪ ነው።

የሣልሳይ ወያነ ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃነ አጽብሃ፤ በሕወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለው ልዩነት ለክልሉ ችግሮች መፍትሔ የመስጠት ዕድሉን አጥብቦታል ብለዋል።

አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት ምንም ዓይነት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን የጠቀሱት ኃላፊው፣ የሥልጣን ጊዜ መራዘሙ የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች አይመልስም ብለዋል።

የትንሳኤ ሥርዓት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ደገፉ ጉደፋይ በበኩላቸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥልጣን መራዘም መፍትሔ እንደማይሆን ገልጸዋል።

በክልሉ ያለውን ችግር ለመፍታት የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ሊቃውንትንና ሲቪክ ማኅበራትን ያካተተ አካታች ጊዜያዊ መንግሥት መቋቋም እንዳለበት አሳስበዋል።

ይህም የሕዝብ ይሁንታ ያለው መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል የመሸጋገሪያ ሕግ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሃለፎም ምርዕ በበኩላቸው፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥልጣኑን ለታጣቂ ኃይሎች አሳልፎ መስጠቱን በመጥቀስ ችግሮችን ለመፍታት አቅም እንደሌለው ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የፌዴራል መንግሥት የወሰነው ውሳኔ ከክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ተገቢ መሆኑን ጠቁመው፤ አሁን ያሉትን አመራሮች በመተካት ሌሎች ቢመረጡ ክልሉ ወደ ባሰ ቀውስ ሊገባ እንደሚችል ያላቸውን ሥጋት  ተናግረዋል።

ፓርቲዎቹ በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩም በቀሪው የሥልጣን ዘመኑ ለሕዝቡ መሠረታዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

(አሐዱ  ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...