“የሟችም የገዳይም እናት እኔ ነኝ”

Date:

​”የሟችም የገዳይም እናት እኔ ነኝ” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ የእምነት እናቶች ሀገራዊ ፈዉስና ሰላምን ለማምጣት የ3 ቀናት ብሔራዊ የንስሀ ጥሪ አስተላለፉ።

​እናቶቹ ሀገሪቱ በአሁን ወቅት ካለችበት ማህበራዊ፣ ሥነ-ምግባራዊ እና ሰብአዊ ቀውስ ወጥታ ዘላቂ ሰላም እንድታገኝ ለአባቶች እና ለሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

በመፈናቀል፣ በሙስና መስፋፋትና በግጭቶች ምክንያት የሚደርሰውን ስቃይ በጋራ እየተጋሩ መሆኑን የገለጹት እናቶቹ፤ “የሟችም የገዳይም እናት እኔው ነኝ” በሚል የእናትነት መንፈስ የችግሩ ሰለባ የሆኑትን ሁሉ ማስታገስና ማዳን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

​በአሁኑ ወቅት ሰብአዊ ማንነት ተንቆ፣ ቋንቋን ጣዖት በማድረግ የሚሰራጩ የጥላቻ ትርክቶች፣ ቂም በቀል እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ሀገርንና ትውልድን እያደሙ እንደሚገኙም በምሬት ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ቀናት ወደ ፈጣሪ የሚጮኹበትና ይቅርታ የሚጠይቁበት ብሔራዊ የ3 ቀናት የጾምና ጸሎት (የንስሐ አዋጅ) በጋራ እንዲታወጅ እናቶች አሳስበዋል።

​የሃይማኖት አባቶች ሀገርን ከጥፋት የመጠበቅና ትዉልድን የማዳን ሀገራዊ መለከት እንዲያወጁም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

​#የሟችምየገዳይምእናትእኔነኝ #የእናትነትመንፈስ #የሰላምጥሪ #ሀገራዊፈውስ #የንስሐአዋጅ #ሰላምለኢትዮጵያ #የእምነትእናቶች #ኢትዮጵያ #PeaceForEthiopia #MothersForPeace #Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...