የትራንስፖርት ቢሮ ጥብቅ የትራፊክ ቁጥጥርና ሕግ ማስከበር ሊጀምር ነው

Date:

የከተማ አስተዳደሩ በአዲሱ የሥልጣንና የተግባር ክፍፍል አዋጅ መሠረት የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን መዋቅርን በማጠፍ፣ ኃላፊነቱን ለትራንስፖርት ቢሮ፣ ለመንገዶች ባለሥልጣንና ለትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል ተከፋፍሎ እንዲሰጥ ማድረጉን አስታወቀ።

በሽግግሩ ወቅት በነበረው የሥራ ርክክብ ምክንያት ላለፉት ጥቂት ቀናት የቁጥጥር ክፍተቶች መፈጠራቸውን ያመለከተው አስተዳደሩ፤ በዚህም የፓርኪንግ ሕግ መጣስ፣ በእግረኞች መብት መጋፋትና ከባድ ተሽከርካሪዎች ከሚፈቀድላቸው ሰዓት ውጭ መንቀሳቀስ የመሳሰሉ ችግሮች መስተዋላቸውን ገልጿል።

የትራንስፖርት ቢሮ የሥራ ርክክብ ሂደቱን ማጠናቀቁን የጠቆመው ማሳሰቢያው፤ ከጥቅምት 13 2019 ዓ.ም ጀምሮ የቢሮው ኦፊሰሮች ከትራፊክ ፖሊስና ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር መደበኛ የቁጥጥርና የሕግ ማስከበር ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለመንገድ ደህንነት ከፍተኛ ቅድሚያ እንደሚሰጥ በመግለጽ፣ የትራፊክ ሕግ የሚጥስ ማንኛውም አሽከርካሪም ሆነ የሕግ አስከባሪ አካል በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን በማስጠንቀቅ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ታጣቂ ኃይሎች ብቻቸውን የሚፈጽሙት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችም ጭምር …

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከምሥረታው አንስቶ ባለፉት 7...

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና...

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...