የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

Date:

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የ10 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ እድገት አፅድቋል።

እድገቱ ምሁራኑ በትምህርትና አካዳሚያዊ አገልግሎት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያስመዘገቧቸውን የላቀ ውጤቶችና አስተዋፅዖዎች መሠረት ያደረገ ነው።

በዚህም መሰረት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ያደጉት ምሁራን፦

1. ዶ/ር አብርሃም ገብሬ ተካለኝ- በስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር

2. ዶ/ር አዳነ ቢተው ተገኘ- በሜዲካል ማይክሮባዮሎጂ ፕሮፌሰር

3. ዶ/ር አደይ ፈለቀ ደስታ- በኢንቫይሮሜንታል ማይክሮባዮሎጂ ፕሮፌሰር

4. ዶ/ር ደሳለኝ ያየህ አያል- በዲሳስተር ሪስክ ማኔጂሜንት ፕሮፌሰር

5. ዶ/ር ኃይለልዑል ንጉሴ ዱባለ- በቨተርነሪ ኢፒዲሞሎጂ ፕሮፌሰር

6. ዶ/ር ካሳ ሚካኤል ወ/የሱስ- በማቲማቲክስ ኢጁኬሽን ፕሮፌሰር

7. ዶ/ር ሰለሞን ገነት ገብሬ- በባዮኬሚስትሪ ፕሮፌሰር

8. ዶ/ር ሰለሞን አረዓያ ካሳ- በጀነራል ኢዱኬሽን ፕሮፌሰር

9. ዶ/ር ያረጋል አሳቤ ላቀ- በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፕሮፌሰር

10. ዶ/ር የድልፋና ሰጠአርጌ መኮንን- በፊዚካል ኬሚስትሪ ፕሮፌሰር

ይህ ስኬት ዩኒቨርሲቲው ለአካዳሚያዊ ልህቀት፣ ለምርምርና ፈጠራ እንዲሁም ለማኅበረሰብ አገልግሎት ያበረከተውንና እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ያለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ከፍተኛው የአካዳሚክ ማዕረግ ለበቃችሁ ምሁራን እንኳን ደስ አላችሁ መልእክቱን አስተላልፏል።

በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው የጀመርነውን የአካዳሚክ፣ ምርምርና አገልግሎት ልቀት ለማምጣት ከመቼውም በላይ እንደምትተጉ በማመን ነው ማለቱን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...

የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ

አርብ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ለታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ...