የአካታች አዋርድ የሽልማት መርሐ ግብር ዛሬ ይካሄዳል

Date:

አካል ጉዳተኝነት የአቅም ገደብ እንዳልሆነ በተግባር በማሳየት በተለያዩ ዘርፎች ስኬት ያስመዘገቡ ዜጎችን ለማበረታታት የተዘጋጀው የመጀመሪያው ዙር “አካታች አዋርድ” የሽልማት መርሐ ግብር ዛሬ በቫምዳስ ሲኒማ ይካሄዳል።

በቱራይዝ መልቲሚዲያ አዘጋጅነት ከቀኑ 8:00 ሰዓት የሚጀምረው መርሐ ግብር፣ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱና አርአያ ለሆኑ አካል ጉዳተኞች እውቅናና ሽልማት የሚሰጥበት መድረክ ነው።

ሽልማቱ በሥራ ፈጠራ፣ በንግድና ኢኮኖሚ፣ በትምህርት፣ በሳይንስና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስፖርት፣ በበጎ አድራጎት፣ በግብርናና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ስኬት ያስመዘገቡ ግለሰቦችን ያካትታል።

በየዓመቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የታለመው ውጥኑ፣ ከሽልማት መርሐ ግብሩ ባለፈ ዘላቂ የማኅበረሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዙ ተግባራትንም ይዟል።

በየሁለት ወሩ በሚዘጋጁ የውይይት መድረኮች፣ አካል ጉዳተኞች የመንገድ፣ የትራንስፖርትና የሕንፃ ተደራሽነት ችግሮችን በማንሳት ለሚመለከታቸው የመንግሥትና የግል ተቋማት የመፍትሔ ሃሳቦች የሚያቀርቡበት ዕድል እንደሚፈጠር አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

በዝግጅቱ ላይ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የጥበብ ሰዎችና በጎ አድራጊዎች በመገኘት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ  ህዳር  19 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን ቆይታ  አምዳችን :- ‹‹ሰዎች ለምን የሕሊና ወንጀል እንደሚሠሩ አይገባኝም›› ኢንጂነር...

ራያ ከሲቲ ጨዋታ በፊት ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ከማንቸስተር...

በኩዌት የድሮን ጥቃት ሁለት ጣሊያናውያን ተገደሉ

ጣሊያን በኩዌት ሁለት ዜጎቿን በገደለው የድሮን ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ...

በየመን ከ700 በላይ ወታደራዊ ጥቃቶች ተፈጸሙ

የየመን መንግሥት ኃይሎች ባለፉት 24 ሰዓታት በሁቲ ታጣቂዎች ይዞታ...